አስቀድሞ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ በልጅነት አዕምሮው ከተረዳው እውነታ የተለየ እውነታ ለማዳመጥም፣ ለመቀበልም ዝግጁ አይደለም፡፡ የሚገርመው ደግሞ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ታሪኩንና ማንነቱን የሚያውቀው ከባህር በማንኪያ ነው። "የሰው ልጅ መንገዱን ይቀጥላል። አንዱ ትውልድ ሌላውን በመከተል ወደ ላይ ይጓዛል።" ይላሉ ሊቁ እጓለ ገብረ ዮሐንስ ነገር ግን የታሪክ ቅብብሎሹ አሁን የላላው የታሪክን ምንነት ካለመረዳት ይመስለኛል። ደራሲና ኀያሲ ዓለማየሁ ገላጋይ V.O. Klyuchevsky MhùR ጠቅሶ እንዲህ ይላል። "ታሪክ ሐይል ነው፡፡ ለህዝቦች ጥሩ እስከሆነላቸው ድረስ ስለምንነቱ በመዘንጋት ፍስሐነቱን ብቻ ለራሳቸው ለማስረዳት ይሞክራሉ፡፡ እንደፈለጉት ባልሆነ መንገድ ሲመጣና መጥፎ ሲሆንባቸው ግን አስፈላጊ አለመሆኑና አለመጥቀሙ ይሰማቸው ይጀምራል።" እንዲህ ነው የሆነው እንዲህ ባለ መወራከብ ውስጥ መኖር የወደፊት ራዕይን ያደበዝዛል። ነጋችንን የሚወስነው የነገው ንፋስ ይሆናል።
የግሪኳ ፊኒክስ (ወፍ) በብዙ ሐይሞኖቶች እንደ ማስተማሪያ ትጠቀሳለች፤ ገጣሚዎች ብዙ ግጥም ገጥመውላታል አንድ መቶ ቀዳዳ ያለው ዋሽንት መሰል ኧፍ አላት በእያንዳንዱ ቀዳዳ መንፈሳዊ ዜማ ትዘምራለች። መሞቻ ጊዜ ሲደርስ ለሬሳዋ መሸከሚያ ታዘጋጃለች አሳዛኝ ዜማም ታንቆረቁራለች ገላዋንም ታቃጥለዋቸለህ እሣቱ ሲያልቅ እንደ አዲስ ትፈጠራች... የራስ የታሪክ ሽግግር አላለም ሽግግሩ በእሳት ነው። ደግሞም ወደ እሳት (ለትንሳኤ) ገጣሚና ፈላስፋ ሰለሞን ደሬሳ የኋላ ታሪካችንን አይቶ ተከታዩን ቅኔ ሰንዝሯል።
"...ከሺህ ዘመን በፊት ያሬድ መቀኘቱ
ዘይገርም ላርባራት ትውልድ መብቃቱ
አላመንም? አልሞትንም? አልተቃጠልንም?
አልቀበርንም? አልወደድንም? አላፈቀርንም?
ውርደትን አልተቀበልንም? አንበቃም ለማዜም?
ሱስ ሆኖ 'ንጂ ከላይ ወደታች መቀነስ
በፖለቲካ፥ በኤኮኖሚ፥ ብቻ ላንታደስ
ምኑ ጠፍቶን
ምኑ ጎድሎን
ሺህ ዘመን ነጻነት ተገመፈፍን
ለቱሪስት አጋፋሪ ልንሆን?"
[ዘበትል እልፊቱ ወለሎታ ገጽ-34]
ይህ የማርክስን አንድ አጭር ልቦ-ለድ ያስታውሰኛል። ታሪኩ እንደዚህ ነው። "…ከእለታት አንድ ቀን …የሆነች ሀገር ወይ መንደር ነዋሪዎች በባህር ላይ ተንሳፍፎ የመጣ አንድ አስከሬንን ከውሃው አውጥተው ወደ መኖሪያቸው ለመቅበር ያስገቡታል፡፡
ከመቅበራቸው በፊት በሞተው የወንድ አስከሬን በጣም ይመሰጣሉ፡፡ በተለይ ሴቶቹ፡፡ ሟቹ በሁሉም ነገሩ እነሱን ይበልጣቸዋል፡፡ የቁመቱ ትልቅነት፣ የትከሻው ስፋት፣ የበድን እጆቹ ጥንካሬ፣ የማይሰራ ጭንቅላቱ ግዙፍነት… ወዘተ--፡፡" ይህ አስከሬን፤ ሞቶ እንኳን ከሕያዎቹ (እነሱ) በጣም የላቀ ነው፡፡ ሞቶም የት እና የት ያጥፋቸዋል፡፡ ምናልባት ሹክ ያላለላቸው ወይ ያልሰጣቸው ቀለም ይኖራል ትላንትን እንዲህ ያስመኛቸው ነገረ-አሁን የሚሰራው ትላንትን ወደዛሬ በማምጣት ነገን በማስቀጠል እንጂ በተአምር አይደለም።
የታሪክ ቅበብሎሹ የላላበት ማህበረሰብ "ደቡብን አልሞ የሚጋልበው ወደ ሰሜን ነው" አንድ የቻይናዎች ተረት ልንገራችሁ:- አንድ ባለጸጋ ደቡብ ክልል ወደምትገኝ አንዲት ወረዳ ለመሄድ ዓልመው፣ በምርጥ ፈረሶቻቸው የሚሳቡ ሠረገላቸውን አዘጋጅተው፣ የበቃ ባለጋሪአቸውን “ተነስ! ቼ በለው!” ብለው ጉዞ ጀመሩ። ጥቂት ምዕራፍ እንደገሰገሱ፣ አንድ እግረኛ ባለፀጋውን ተጓዥ ያቆማቸውና፣ “ሰላም፣ ጌታው! ወዴት ነው የምገሰግሱት?” አላቸው። "ወደደቡባዊቷ ገነት ወደ ኤዞ!” አሉ ባለፀጋው ተጓዥ። “ኤዞ’ኮ እርሶ እንዳሉት ደቡብ ውስጥ ናት። እርሶ ግን እየሄዱ ያሉት ወደሰሜን ነው፤” ቢላቸው። “አውቃለሁ! ፈረሶቼ በፍጥነት እና በብርታታቸው የሚያህላቸው የለም። ኤዞ መድረሴ አይቀርም!” አሉ ሰውዬው በልበ-ሙሉነት። መንገደኛውም ግራ በመጋባት፣ “ግን’ኮ ጌታው፣ እየሄዱ ያሉበት አቅጣጫ ከመድረሻዎ ተቃራኒ በመሆኑ ፈረሶቾ ፈጣንና ብርቱ በሆኑ ቁጥር ከዓላማዎ ይበልጥ ያርቅዎታል እንጂ ወደ ዓላማዎ አያቀርብዎትም!” አለ። "ሰውዬው፣ ባለጋሪዬንስ አታውቀውም? የዓመታት ልምድ ያለው፣ የበቃና የነቃ ባለጋሪ’ኮ ነው፤” አሉ ባለፀጋው ተጓዥ፣ ትዕግስታቸው እየተሟጠጠ። “ቢሆንም ጌታው፣ ወደሰሜን የሚወስዶ ባለጋሪ ምን ብቁ ቢሆን እንዴት ከደቡባዊቷ ኤዞ ያደርሶታል?” ሞገታቸው መንገደኛው። "አንተ ደሞ! የያዝኩትን ስንቅና ትጥቅስ አታይም? የመንገዱን ቀናነትስ ልብ አላልክም? እንዴት ነው ይህን የመሰለ መንገድ ኤዞ አያደርስህም የምትለኝ?” አሉ ተጓዡ። መንገደኛውም፣ "ደቡብን ዓልመው ሰሜን የሚነጉዱ፣ ታሰቡት አይደርሱም፣ ሺ አድማስ ቢቀዱ!” ብሎ፣ በመንዙማ ስልት አዜመላቸው። ሰውዬውም፣ “አንተ ሰነፍ አሳናፊ! ከዓላማዬ የሚያስቀረኝ አቅጣጫዬ ሳይሆን ያንተ ሺ ጥያቄና አጉል ዝማሬ ነው። በል፣ ከመንገዴ ዞር በልልኝ! ሟርተኛ!” ብለው በጀመሩት አቅጣጫ መጋለባቸውን ቀጠሉ። የት ይደርሱ ይሆን? አቅጣጫ ሳይቀበሉ። በገጣሚና ፈላስፋ ሰለሞን ደሬሳ ቅኔ ልሰናበት ‘’ብልጠት’’ ሁለት እርምጃ ወደፊት/ ሥስት የዃሊት/ ሳያበረክቱ እልፊት
#ሀገር አማን ቅጽ ሰላሳ