ከሰፊው የጥበብ ማዕድ - ጌታመሳይ ወንደሰን

ከሰፊው የጥበብ ማዕድ፣ ከሙዚቃ መንደር፣  ከአራቱ የኢትዮጵያ ቅኝቶች አምባ ዘልቀን  በግርድሱ ዳሰስ ዳሰስ ለማድረግ እንሞክር ሀገራችን ኢትዮጵያ በግልፅ የምትታወቅበት  በአራቱ ድንቅ ቅኝቶቿ ነው፡፡ እነሱም ትዝታ፣  አምባሰል፣ ባቲና አንቺሆዬ ናቸው፡፡ በእነዚህ ድንቅ  ቅኝቶች ላይ ተንተርሰን በግርድሱ ለመዳሰስ  ከመሞከራችን በፊት ጥያቄ ማስቀደም አሰብኩ፡፡ ጥያቄ፡- በጥቅሉ አለም ላይ ስንት ድምፆች አሉ . . . ሆኖም እንደ ጥያቄው አስፈላጊነት ዙሪያ  በህብረት ውይይት መነጋገር እንችላለን ፡፡ ላሁን  ግን ከላይ በቅኝቶች ዙሪያ ወዳነሳሁት ሃሳቤ  መመለስ ፈለኩ፡፡ 
አንደሚታወቀው በአለም ላይ  ካሉት ድምፆች ውስጥ አራቱ ቅኝቶቻችን በአንድ  ዜማ ላይ (5) አምስት ድምፆችን /ፔንታቶኒክ/  ብቻ ይጠቀማሉ፡፡ ይህ ማለት የኢትዮጲያ  በብዛት የሚታወቅ በ5 ድምጾች (ፔንታቶኒክ)  ነው ወደሚለው ድምዳሜ ላይ ያደርሰናል፡፡ ይህ በእንዲህ ይባል እንጂ በጥናት የጠደገፈ  ግኝት ባይሰራለትም ወደ ደቡቡ የሃገራችን ክፍል  ያሉትን ሙዚቃዎች ብንዳስስ ከአራቱ ቅኝቶች  የዘለለ ሌላ ቅኝት እንደሚኖር እርግጥ ነው፡፡  ይቺን አጭር የቅኝት ፅሁፍ ግልፅ ለማድረግ ያህል  ከሙዚቃ መሳሪዎች ውስጥ ፒያኖ ወይም ኪቦርድ  ተጠቅመን C-MAJOR እና C-MINOR ላይ አራቱን ቅኝቶች እንፈልግ፡፡ c-MAJOR :-C-D-E-F-G-A-B-C ENGLISH DO-RE-ME-FA-SO-LA-SI ITALIY  C-MINOR:- C-D-Eb-F-G-A-B-C የሚለውን  ፍሬ ሀሳብ ለማወቅ ግድ ይለናል፡፡ ግልጽ ለማድረግ  ያህል በሙዚቃ ቋንቋ (# sharp) ምልክትን  ከፊደሎቹ አናት ላይ ተቀምጠው ካገኘናቸው  ነገር ግን ደግሞ ምልክቱ በነበረን ድምፅ ላይ  ግማሽ መጨመር እንዳለብን እየነገረን ነው፡፡ ነገር ግን ደግሞ ምልክቱ b(flat) ከሆነ ወደ ኋላ ግማሽ ድምፅ እንቀንሳለን ማለት ነው፡፡  
ይህ በእንዲህ እናዳለ ለአሁን ከአንጋፋው  ቅኝታችን ከትዝታ ቤተሰብ ደርሰን እንመለስ፡፡ የትዝታ ቅኝት በሁለት ቤተሰብ ተከፍሎ እናገኘዋለን፡፡ ሜጀር ትዝታና / MAJOR / ማይነር ትዝታ / MINOR / ናቸው፡፡ ከላይ በተገለፀው መሰረት ማንኛውንም ሜጄር  ቅኝት ሜጀር ስኬሉ ላይ ማይነር ቅኝቱን ደግሞ  ማይር ስኬል / minor scale / ላይ ይገኛል፡፡ በዚህ  መሰረት ሜጀር ትዝታን (major s) ለመጫወት  ስንፈልግ የሜጀር ስጀር ስኬሉን አራተኛና  ሰባተኛውን ድምፅ እንዘላለን፡፡ ይህ ማለት  ከላይ ለአብነት ያህል ብለን ያስቀመጥነውን ሲ ሜጀር ስኬል ስንመለከት ከተከታታይ ድምጾች  ውስጥ F ( fa ) እና B ( si ) እናስወግዳለን፡፡ ለምሳሌ በዚህ ቅኝት ላይ የተሰፉ ሙዚቃዎን  ስናይ “የሺሃረጊቱ” የሚለው የመሃሙድ አህመድ ዜማና ሌሎችም እንዲሁም በቅርቡ አልበሞቹን ያስደመጠን ዳዊት ፅጌ አብዛኛዎቹ  ሙዚቃዎች በዚህ ቅኝት ላይ የተቀኙ ናቸው፡፡  
በማስከተል ማይነር ትዝታን ለመጫወትና  በቀላሉ ለመረዳት ሜጀር ትዝታ ላይ ያሉት  ድምጾች እንዳሉ ሆነው 3ተኛውና 5ተኛውን  ድምፅ በግማሽ ድምፅ ወደ ኋላ ይቀንሳል፡፡ ይህ ማለት C-MAJOR C-D-E-F-G-A--C ) ትዝታ  ሲሆን C-MINOR:- ትዝታ ደግሞC-D-Eb-FG-Ab-C ይሆናል ማለት ነው፡፡ በዚህ ቅኝት  ላይ የተሰሩ ሙዚቃዎችን ስንመለከት ከአለማየሁ  እሸቴ ሙዚቃዎች ውስጥ እትቱ በረደኝ እና ሌሎችም፤ እንዲሁም ከዳዊት ፅጌ ሙዚቃዎች  ውስጥ እትቱ የተሰኘው ነጠላ ዜማን እናገኛለን፡፡ እስካሁን የትዝታ ቤተሰብን በስሱ  ለማየት ሞክረናል፡፡   
 
“Music is an art of organized sound``. The formal design of a piece of music also contributes to its beauty and value Source the book of music,’’ the arts of listening by Jean Ferris አንደተለመደው ዛሬም ወደ ሃገራችን ኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ ደማቅና አብረቅራቂ  አሻራቸውን ካሳረፉ ታላቅ የሙዚቃ ሰዎች መካከል አርቲስት ሙላቱ አስታጥቄ ማናቸው? ምን  ሰርተው አለፉ ለሚለው ጥያቄ ምላሻችን ምን ይሆን? በመቀጠል ግን በከፍል አንድ ዳሰሳ ቅኝት ላይ” በጥቅሉ በአለም ላይ ስንት ድምፆች አሉ? የሚል  ጥያቄ አንስቼ ነበር፡፡ አስታውሳለሁ በመሆኑም በአለም ላይ 12 ድምፆች ብቻ ይገኛሉ፡፡ ይህ  ማለት በእንስሳቶች፣ በእፀዋቶ፣ በሰዎችና በግዑዛን አካላት መካከል የሚፈጠሩ ድምፆችን በሙሉ  ያካትታል፡፡ እንደሚታወቀው ከዚህ በፊት ከኢትዮጵያ አራት ቅኝቶች ውስጥ tizita major እና tizeta minor የሆኑትን በስሱ ዳሰስ አርገን ተመልክተናል፡፡ ከዚህ በማስከተል ደግሞ አንጋፋውና ተወዳጁን አምባሰል ቅኝትን እንመለከታለን፡፡ አምባሰል ቅኝት እንደትዝታ ሁሉ major እና minor ተብሎ በሁለት ቤተሰቦች ይመደባል፡፡ ለአብነት  ያህል እንዚህን ቅኝቶች በ D major እና minor scale እንያቸው  D major scale :- D E F# G A B C# D ሲሆን ከዚህ major scale አምባሰልን ለማግኘት  ሶስተኛውን (F#) እና ሰባተኛውን (c#) ዘለን በሌሎች መጫወት ስንችል ነው፡፡ ይህ ማለት D E G A B D ድምፆች አምባሰል ሜጀር ቅኘትን ያስደምጡናል፡፡ ሁለተኛው የአምባሰል ቤተሰብ የሆነው ደግሞ አምባሰል ማይነር ሲሆን D ማይነር ስኬል ላይ  እንገኘዋለን፡፡  D ማይነር ስኬል:- D E F G A Bb C D ሲሆን ከዚህ ማይነር ስኬል ላይ እናገኘዋለን፡፡ ከዚህ Minor scale ላይ Ambaseel minor ለመጫወት 3ተኛውንና 7ተኛውን ድምፆች ይዘልና  ከ ሁለተኛው 6ተኛው ድምፆች ላይ ወደ ኋላ በግማሽ Bb ተቀንሶ ይቃኛል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ  ቀሪዎቹን ሁለት ቅኝቶች ባቲና አንቺ ሆዬ በቀጣይ የቅኝት ዳሰሳ ላይ እንተዋወቃቸዋለን፡፡ መልካሙን  ሁሉ ተመኘሁ፡፡ ቸር እንሰንብት

© Demera Media and Communication. All rights reserved
Website By: Alen & Amanuel