የምሁራን፣ወጣቱ ትውልድና ማህበራዊ መገናኛ ብዙሀን በቀጣይ ማድረግ ስለሚገባቸው ሚና አስመልክቶ የአሰልጣኞች ስልጠና

Start Date
End Date
Location
Addis Ababa, Ethiopia

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሀገሪቱ በቀጣይ የሚደረገው ምርጫ ዲሞክራሲያዊ ተአማኒና ተቀባይነት ያለው እንዲሆንና በሀገራችን ኢትዮጵያ የዲሞክራሲ ስርአት እንዲገነባ ለማስቻል ምሁራን፣ወጣቱ ትውልድና ማህበራዊ መገናኛ ብዙሀን በቀጣይ ማድረግ ስለሚገባቸው ሚና አስመልክቶ የአሰልጣኞች ስልጠና በቢሾፍቱ ከተማ ተካሂዷል፡፡

ደመራ ሚዲያ እና ኮምኒኬሽን ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ይህ ስልጠና ከተለያዩ ዩንቨርስቲዎች የተውጣጡ ምሁራን እንዲሁም ባለድርሻ አካላትን አሳትፏል፡፡

በስልጠናው ሊህቃን እንደ ሊህቃንነታቸው ጠንካራ እና ለሀገሪቱ ፋይዳ ይኖራቸዋል ያሏቸውን ሀሳቦች የማቅረብ ተግባርን መወጣት እንዳለባቸው ሲገለጽ በምርጫው ሂደት ለሀገሪቱ የሚጠቅመው ሀሳቦች ዙሪያ በመንሸራሸር ሊገጥሙ ለሚችሉ ፈተናዎች የመፍትሄ አማራጮችን አስቀምጠዋል፡፡

በተጓዳኙም የመራጭ እንዲሁም ዝምተኛው ብዙኃን ንቁ እና አዎንታዊ ተሳትፎ በማድረግ ከፍተኛ ሚና ሊጫወቱ በሚችሉባቸው መንገዶች ዙሪያ ሀሳብ ያነሳው መድረክ በሀገር ግንባታ ዙሪያ ወጣቶች በምርጫው ሂደት በሚያደርጉት ተሳትፎ ስለሚያበረክቱት ፋይዳ ሰፊ ዳሰሳ ተሰጥቷል፡፡

ማህበራዊ ሚዲያ በመጪው ምርጫ የሚኖረው ተጽእኖ፣ መረጃ ስለማጣራትና ለህዝብ ስለማድረስ እንዲሁም በተለያዩ አካላቶች(ማህበረሰብ፣ የፖለቲካ ሊህቃን፣ ምሁራን እና ባለድርሻ አካላት) ማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀማቸው እንዴት መምሰል እና በምን አይነት ሀላፊነት ውስጥ መረጃን ማጋራት አለባቸው ስለሚለው ሀሳብ በስልጠናው የተነሳ ሌላኛው አርእስተ ጉዳይ ሆኗል፡፡

ግንቦት 7 የጀመረው የአሰልጣኞች ስልጠና በዛሬው እለት በስኬት ተጠናቋል፡፡

© Demera Media and Communication. All rights reserved
Website By: Alen & Amanuel