ሀገር ምን ትሻለች 2?

Start Date
End Date
Location
National Theatre, Addis Ababa Ethiopia

ደመራ ሚዲያ እና ኮምኒኬሽን (ሚያዝያ 27 2021) ፡ "ሀገር ምን ትሻለች 2?" በሚል መሪ ቃል አንጋፋ እና እውቅ የጥበብ ሰዎች የተሳተፉበት ዝግጅት በብሔራዊ ቴያትር ተካሂዷል።

ሀገራችን ያለችበት ነባራዊ ሁኔታን አስመልክቶ በመድረኩ ጥበብን የተላበሱ ወቅታዊ ዝግጅቶች ቀርበውበታል፤ መሳጭ ዲስኩሮች፣ መጣጥፍ እንዲሁም ለሰሚው ማራኪ የሆኑ ግጥሞችም እንዲሁ።

ሚያዝያ 27 ማምሻውን በተካሄደው መርሐግብር መጋቤ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ፣ ዶ/ር ወዳጄነህ ማሐረነ፣ አርክቴክት ዮሐንስ መኮንን (ከኢዜማ)፣ ደራሲና ገጣሚ በቀለ ወያን ጨምሮ ሌሎች የጥበብ እንግዶች በመድረኩ ስራዎቻቸውን አቅርበዋል።

"ሀገር ምን ትሻለች?" በምስክር ጌታነው ሚዲያና ፕሮሞሽን ተዘጋጅቶ በደመራ ኮሙኒኬሽን ሚዲያ አጋርነት የሚቀርብ ወርዊ የስነ-ጥበብ መርሐግብር ነው።

ያላወቅነውን እንድናውቅ፣ የጥበብ እውቀትን እንድንቀስም ዘንድ ጥበበኞችን ወደኛ እናቀርባለን!


በዝግጅቱ ላይ የነበሩ ሁነቶችን በተንቀሳቃሽ ምስል ለመከታተል የደመራን የዩቲዩብ ድህረ-ገጽ አማራጭ አድርጉ፤ ለተጨማሪ ምስሎች እንዲሁ የፌስቡክ፣ ትዊተር እንዲሁም ቴሌግራም ገፃችን ተከታዮች በመሆን ተጨማሪውን ይመልከቱ፡፡


ፌስቡክ https://www.facebook.com/EngageandEnlighten 
ትዊተር https://mobile.twitter.com/Demeramedia1
ዩቲዩብ https://youtu.be/GFvbazRd6Os
ቴሌግራም https://t.me/Demeramediaandcommunication

© Demera Media and Communication. All rights reserved
Website By: Alen & Amanuel